የፌደራል ሴቶች ክንፍ ምክር ቤት አባልና የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ ጽ/ቤት ኃላፊ ክብርት ነኢማ ሙኒር በጋሞ ዞን የሴቶች ክንፍ ኢንተርፕራይዝ ስራ አስጀምረዋል።
አርባምንጭ፤ የካቲት 9/2018ዓ/ም(ጋሞ ቴሌቪዥን)፦
በጋሞ ዞን የሴቶች የልማት እንቅስቃሴን እየጎበኙ የሚገኙት የፌደራል ሴቶች ክንፍ ምክር ቤት አባልና የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ ጽ/ቤት ኃላፊ ክብርት ነኢማ ሙኒር የሴቶች ኢንተርፕራይዝ አካል የሆነውን የአትክልትና ፍራፍሬ ግብይትና ዶሮ እርባታ ስራ በብርብር ከተማ አስተዳደር አስጀምረዋል።
በመርሃግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና ማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ምህረት በላይ፣ የጋሞ ዞን የህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት አለሚቱ ዮሴፍ፣ የጋሞ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪና ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን ኢዩኤል፣ የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ደመረና የብርብር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብርሃም አይካ ተግኝተዋል።



