የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ምክር ቤት ጉባኤ የዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ተጠናቀቀ
አርባምንጭ፤ የካትት 7/2018 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቭዥን፡፡የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ተኛ ዙር 5ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ተኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ ፍረድ ቤት የቀረበለትን የዳኞች ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል።የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍርድቤት ፕረዚዳንት አቶ ቦጋለ ፈይሳ ለዞን፣ ለወረዳ እና ለከተማ አስተዳደር እጩ የሆኑ 74 የፍርድቤት ዳኞች ሹመት አቅርበዋል።ዳኞቹ ለህገመንግስቱ ታማኝ የሆኑ በታታሪነታቸውና በስነምግባራቸው ለእጩነት የቀረቡ መሆናቸውን ተገልፆ በዳኝነት ሙያ ለመሰማራት ፍቃደኛ መሆናቸው ተጠቅሷል።
ባላቸው የህግ እውቀት እና ልምድ መሠረት መመረጣቸውን ገልጸው በክልሉ የተዘጋጀውንም የህግ ማሻሻ ስልጠና የወሰዱ መሆናቸውም ተገልጿል።የምክር ቤቱ አባላት የቀረቡላቸውን የዳኞች ሹመቶች መርምሮ በሙሉ ድምፅ ያፀደቁ ሲሆን ዳኞቹ በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን መደበኛ ጉባኤ አጠናቋል።



